- 
			
				
- 
									
   Amharic (NT)									 - 
									
									 
- 
									
									11
									 
									 
									|2 Corintios 3:11|
									ያ ይሻር የነበረው በክብር ከሆነ፥ ጸንቶ የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ሆኖአልና።									
									    
								 
- 
									
									12
									 
									 
									|2 Corintios 3:12|
									እንግዲህ እንዲህ ያለ ተስፋ ካለን እጅግ ገልጠን እንናገራለን፥									
									    
								 
- 
									
									13
									 
									 
									|2 Corintios 3:13|
									የዚያንም ይሻር የነበረውን መጨረሻ ትኵር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ በፊቱ መጋረጃ እንዳደረገ እንደ ሙሴ አይደለንም።									
									    
								 
- 
									
									14
									 
									 
									|2 Corintios 3:14|
									ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ። ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና።									
									    
								 
- 
									
									15
									 
									 
									|2 Corintios 3:15|
									ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤									
									    
								 
- 
									
									16
									 
									 
									|2 Corintios 3:16|
									ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል።									
									    
								 
- 
									
									17
									 
									 
									|2 Corintios 3:17|
									ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።									
									    
								 
- 
									
									18
									 
									 
									|2 Corintios 3:18|
									እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።									
									    
								 
 - 
									
 - 
				
Sugerencias
 

Haga clic para leer Juan 16-18