-
-
Amharic (NT)
-
-
7
|2 Corintios 13:7|
ክፉ ነገርንም ከቶ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ እኛ የምንበቃ ሆነን እንገለጥ ዘንድ አይደለም ነገር ግን እኛ ምንም እንደማንበቃ ብንሆን፥ እናንተ መልካሙን ታደርጉ ዘንድ ነው።
-
8
|2 Corintios 13:8|
ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና።
-
9
|2 Corintios 13:9|
እኛ ስንደክም እናንተም ኃይለኞች ስትሆኑ ደስ ብሎናልና፤ እናንተ ፍጹማን ትሆኑ ዘንድ ለዚህ ደግሞ እንጸልያለን።
-
10
|2 Corintios 13:10|
ስለዚህ ጌታ ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ እንደ ሰጠኝ ሥልጣን፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በቁርጥ እንዳልሠራ በሩቅ ሆኜ ይህን እጽፋለሁ።
-
11
|2 Corintios 13:11|
በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፥ ምክሬን ስሙ፥ በአንድ ልብ ሁኑ፥ በሰላም ኑሩ፥ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
-
12
|2 Corintios 13:12|
በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ።
-
13
|2 Corintios 13:13|
ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
-
14
|2 Corintios 13:14|
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Jueces 4-5