-
-
Amharic (NT)
-
-
20
|Juan 11:20|
ማርታም ኢየሱስ እንደ መጣ በሰማች ጊዜ ልትቀበለው ወጣች፤ ማርያም ግን በቤት ተቀምጣ ነበር።
-
21
|Juan 11:21|
ማርታም ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር፤
-
22
|Juan 11:22|
አሁንም ከእግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሰጥህ አውቃለሁ አለችው።
-
23
|Juan 11:23|
ኢየሱስም። ወንድምሽ ይነሣል አላት።
-
24
|Juan 11:24|
ማርታም። በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንዲነሣ አውቃለሁ አለችው።
-
25
|Juan 11:25|
ኢየሱስም። ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤
-
26
|Juan 11:26|
ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።
-
27
|Juan 11:27|
እርስዋም። አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው።
-
28
|Juan 11:28|
ይህንም ብላ ሄደች እኅትዋንም ማርያምን በስውር ጠርታ። መምህሩ መጥቶአል ይጠራሽማል አለቻት።
-
29
|Juan 11:29|
እርስዋም በሰማች ጊዜ ፈጥና ተነሣች ወደ እርሱም መጣች፤
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 1 Corintios 11-13