-
Leer por capítulos:
-
Amharic (NT)
-
-
11
|Mateo 25:11|
በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና። ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ።
-
12
|Mateo 25:12|
እርሱ ግን መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ።
-
13
|Mateo 25:13|
ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።
-
14
|Mateo 25:14|
ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤
-
15
|Mateo 25:15|
ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ።
-
16
|Mateo 25:16|
አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤
-
17
|Mateo 25:17|
እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ።
-
18
|Mateo 25:18|
አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።
-
19
|Mateo 25:19|
ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው።
-
20
|Mateo 25:20|
አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 2 Corintios 5-7