-
-
Amharic (NT)
-
-
1
|Romanos 4:1|
እንግዲህ በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም ምን አገኘ እንላለን?
-
2
|Romanos 4:2|
አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም።
-
3
|Romanos 4:3|
መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።
-
4
|Romanos 4:4|
ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፤
-
5
|Romanos 4:5|
ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።
-
6
|Romanos 4:6|
እንደዚህ ዳዊት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን ስለሚቆጥርለት ስለ ሰው ብፅዕና ይናገራል እንዲህ ሲል።
-
7
|Romanos 4:7|
ዓመፃቸው የተሰረየላቸው ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፤
-
8
|Romanos 4:8|
ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው።
-
9
|Romanos 4:9|
እንግዲህ ይህ ብፅዕና ስለ መገረዝ ተነገረ? ወይስ ደግሞ ስለ አለመገረዝ? እምነቱ ለአብርሃም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት እንላለንና።
-
10
|Romanos 4:10|
እንዴት ተቆጠረለት? ተገርዞ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይገረዝ? ተገርዞስ አይደለም፥ ሳይገረዝ ነበር እንጂ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 1 Corintios 8-10