-
-
Amharic (NT)
-
-
2
|Romanos 10:2|
በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና።
-
3
|Romanos 10:3|
የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።
-
4
|Romanos 10:4|
የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።
-
5
|Romanos 10:5|
ሙሴ ከሕግ የሆነውን ጽድቅ የሚያደርገው ሰው በእርሱ በሕይወት እንዲኖር ጽፎአልና።
-
6
|Romanos 10:6|
ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል። በልብህ። ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤
-
7
|Romanos 10:7|
ወይም። በልብህ። ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው።
-
8
|Romanos 10:8|
ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው።
-
9
|Romanos 10:9|
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤
-
10
|Romanos 10:10|
ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።
-
11
|Romanos 10:11|
መጽሐፍ። በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 1 Corintios 8-10