- 
			
				
- 
									
   Amharic (NT)									 - 
									
									 
- 
									
									1
									 
									 
									|Santiago 3:1|
									ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ብዙዎቹ አስተማሪዎች አይሁኑ፥ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃላችሁና።									
									    
								 
- 
									
									2
									 
									 
									|Santiago 3:2|
									ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።									
									    
								 
- 
									
									3
									 
									 
									|Santiago 3:3|
									እነሆ፥ ፈረሶች ይታዘዙልን ዘንድ ልጓም በአፋቸው ውስጥ እናገባለን፥ ሥጋቸውንም ሁሉ እንመራለን።									
									    
								 
- 
									
									4
									 
									 
									|Santiago 3:4|
									እነሆ፥ መርከቦች ደግሞ ይህን ያህል ታላቅ ቢሆኑ በዐውሎ ነፋስም ቢነዱ፥ የመሪ ፈቃድ ወደሚወደው ስፍራ እጅግ ታናሽ በሆነ መቅዘፊያ ይመራሉ።									
									    
								 
- 
									
									5
									 
									 
									|Santiago 3:5|
									እንዲሁም አንደበት ደግሞ ትንሽ ብልት ሆኖ በታላላቅ ነገር ይመካል። እነሆ፥ ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል።									
									    
								 
- 
									
									6
									 
									 
									|Santiago 3:6|
									አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።									
									    
								 
- 
									
									7
									 
									 
									|Santiago 3:7|
									የአራዊትና የወፎች የተንቀሳቃሾችና በባሕር ያለ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል፥ ደግሞ ተገርቶአል፤									
									    
								 
- 
									
									8
									 
									 
									|Santiago 3:8|
									ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው።									
									    
								 
- 
									
									9
									 
									 
									|Santiago 3:9|
									በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን፤									
									    
								 
- 
									
									10
									 
									 
									|Santiago 3:10|
									ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።									
									    
								 
 - 
									
 - 
				
Sugerencias
 

Haga clic para leer Juan 16-18