- 
			
				
- 
									
   Amharic (NT)									 - 
									
									 
- 
									
									11
									 
									 
									|Santiago 5:11|
									እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፥ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።									
									    
								 
- 
									
									12
									 
									 
									|Santiago 5:12|
									ከሁሉም በፊት፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ በሰማይ ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሐላም ቢሆን በምንም አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ ነገራችሁ አዎን ቢሆን አዎን ይሁን፥ አይደለምም ቢሆን አይደለም ይሁን።									
									    
								 
- 
									
									13
									 
									 
									|Santiago 5:13|
									ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር።									
									    
								 
- 
									
									14
									 
									 
									|Santiago 5:14|
									ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።									
									    
								 
- 
									
									15
									 
									 
									|Santiago 5:15|
									የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።									
									    
								 
- 
									
									16
									 
									 
									|Santiago 5:16|
									እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።									
									    
								 
- 
									
									17
									 
									 
									|Santiago 5:17|
									ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥									
									    
								 
- 
									
									18
									 
									 
									|Santiago 5:18|
									ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች።									
									    
								 
- 
									
									19
									 
									 
									|Santiago 5:19|
									ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ማንም ከእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው፥									
									    
								 
- 
									
									20
									 
									 
									|Santiago 5:20|
									ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን፥ የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ።									
									    
								 
 - 
									
 - 
				
Sugerencias
 

Haga clic para leer Juan 16-18