-
-
Amharic (NT) -
-
1
|João 7:1|
ከዚህም በኋላ ኢየሱስ አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበር በይሁዳ ሊመላለስ አይወድም ነበርና በገሊላ ይመላለስ ነበር።
-
2
|João 7:2|
የአይሁድም የዳስ በዓል ቀርቦ ነበር።
-
3
|João 7:3|
እንግዲህ ወንድሞቹ። ደቀ መዛሙርትህ ደግሞ የምታደርገውን ሥራ እንዲያዩ ከዚህ ተነሣና ወደ ይሁዳ ሂድ፤
-
4
|João 7:4|
ራሱ ሊገለጥ እየፈለገ በስውር የሚሠራ የለምና። እነዚህን ብታደርግ ራስህን ለዓለም ግለጥ አሉት።
-
5
|João 7:5|
ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ነበርና።
-
6
|João 7:6|
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። ጊዜዬ ገና አልደረሰም፥ ጊዜያችሁ ግን ዘወትር የተመቸ ነው።
-
7
|João 7:7|
ዓለም እናንተን ሊጠላ አይቻለውም፤ እኔ ግን ሥራው ክፉ መሆኑን እመሰክርበታለሁና እኔን ይጠላኛል።
-
8
|João 7:8|
እናንተ ወደዚህ በዓል ውጡ፤ እኔስ ጊዜዬ ገና ስላልተፈጸመ ወደዚህ በዓል ገና አልወጣም።
-
9
|João 7:9|
ይህንም አላቸውና በገሊላ ቀረ።
-
10
|João 7:10|
ወንድሞቹ ግን ወደ በዓሉ ከወጡ በኋላ በዚያን ጊዜ እርሱ ደግሞ በግልጥ ሳይሆን ተሰውሮ ወጣ።
-
-
Sugestões

Clique para ler Apocalipse 21-21