- 
			
				
- 
									
   Amharic (NT)									 - 
									
									 
- 
									
									21
									 
									 
									|2 Corintios 11:21|
									ደካሞች መስለን እንደ ነበርን በውርደት እላለሁ። ነገር ግን በሞኝነት እላለሁ፤ ማንም በሚደፍርበት እኔ ደግሞ እደፍርበታለሁ።									
									    
								 
- 
									
									22
									 
									 
									|2 Corintios 11:22|
									ዕብራውያን ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ። የእስራኤል ወገን ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ። የአብርሃም ዘር ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ። የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸውን?									
									    
								 
- 
									
									23
									 
									 
									|2 Corintios 11:23|
									እንደ እብድ ሰው እላለሁ፤ እኔ እበልጣለሁ፤ በድካም አብዝቼ፥ በመገረፍ አብዝቼ፥ በመታሰር አትርፌ፥ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ።									
									    
								 
- 
									
									24
									 
									 
									|2 Corintios 11:24|
									አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ።									
									    
								 
- 
									
									25
									 
									 
									|2 Corintios 11:25|
									ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወገርሁ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰበረ፤ ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖርሁ።									
									    
								 
- 
									
									26
									 
									 
									|2 Corintios 11:26|
									ብዙ ጊዜ በመንገድ ሄድሁ፤ በወንዝ ፍርሃት፥ በወንበዴዎች ፍርሃት፥ በወገኔ በኩል ፍርሃት፥ በአሕዛብ በኩል ፍርሃት፥ በከተማ ፍርሃት፥ በምድረ በዳ ፍርሃት፥ በባሕር ፍርሃት፥ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርሃት ነበረብኝ፤									
									    
								 
- 
									
									27
									 
									 
									|2 Corintios 11:27|
									በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርሁ።									
									    
								 
- 
									
									28
									 
									 
									|2 Corintios 11:28|
									የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።									
									    
								 
- 
									
									29
									 
									 
									|2 Corintios 11:29|
									የሚደክም ማን ነው፥ እኔም አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው፥ እኔም አልናደድምን?									
									    
								 
- 
									
									30
									 
									 
									|2 Corintios 11:30|
									ትምክህት የሚያስፈልግ ከሆነ፥ ከድካሜ በሚሆነው ነገር እመካለሁ።									
									    
								 
 - 
									
 - 
				
Sugerencias
 

Haga clic para leer Juan 16-18