- 
			
				
- 
									
   Amharic (NT)									 - 
									
									 
- 
									
									14
									 
									 
									|2 Corintios 8:14|
									የእነርሱ ትርፍ ደግሞ የእናንተን ጉድለት እንዲሞላ በአሁኑ ጊዜ የእናንተ ትርፍ የእነርሱን ጉድለት ይሙላ፤ በትክክል እንዲሆን፥ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ።									
									    
								 
- 
									
									15
									 
									 
									|2 Corintios 8:15|
									ብዙ ያከማቸ አላተረፈም፥ ጥቂትም ያከማቸ አላጎደለም።									
									    
								 
- 
									
									16
									 
									 
									|2 Corintios 8:16|
									ነገር ግን በቲቶ ልብ ስለ እናንተ ያንን ትጋት የሰጠ አምላክ ይመስገን፤									
									    
								 
- 
									
									17
									 
									 
									|2 Corintios 8:17|
									ምክራችንን ተቀብሎአልና፥ ትጋት ግን ስለ በዛበት ወዶ ወደ እናንተ ይወጣል።									
									    
								 
- 
									
									18
									 
									 
									|2 Corintios 8:18|
									ከእርሱም ጋር ስለ ወንጌል ስብከት በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም እንልካለን፤									
									    
								 
- 
									
									19
									 
									 
									|2 Corintios 8:19|
									ይህም ብቻ አይደለም ነገር ግን የጌታን የራሱን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግለው በዚህ ቸር ሥራ ከእኛ ጋር እንዲጓደድ በአብያተ ክርስቲያናት ደግሞ ተመረጠ።									
									    
								 
- 
									
									20
									 
									 
									|2 Corintios 8:20|
									ስለምናገለግለው ስለዚህ ለጋስ ስጦታ ማንም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን፤									
									    
								 
- 
									
									21
									 
									 
									|2 Corintios 8:21|
									በጌታ ፊት ብቻ ያይደለ ነገር ግን በሰው ፊት ደግሞ መልካም የሆነውን እናስባለንና።									
									    
								 
- 
									
									22
									 
									 
									|2 Corintios 8:22|
									ብዙ ጊዜም በብዙ ነገር መርምረን ትጉ እንደ ሆነ ያገኘነውን፥ አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ የሚሆነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር እንልካለን።									
									    
								 
- 
									
									23
									 
									 
									|2 Corintios 8:23|
									ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር ስለ እናንተ አብሮኝ የሚሠራ ባልንጀራዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችን የሚጠይቅ ቢኖርም የአብያተ ክርስቲያናት መልእክተኞችና የክርስቶስ ክብር ናቸው።									
									    
								 
 - 
									
 - 
				
Sugerencias
 

Haga clic para leer Juan 16-18