-
-
Amharic (NT)
-
-
11
|Juan 6:11|
ኢየሱስም እንጀራውን ያዘ፥ አመስግኖም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው እንዲሁም ከዓሣው በፈለጉት መጠን።
-
12
|Juan 6:12|
ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን። አንድ ስንኳ እንዳይጠፋ የተረፈውን ቍርስራሽ አከማቹ አላቸው።
-
13
|Juan 6:13|
ሰለዚህ አከማቹ፥ ከበሉትም ከአምስቱ የገብስ እንጀራ የተረፈውን ቍርስራሽ አሥራ ሁለት መሶብ ሞሉ።
-
14
|Juan 6:14|
ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ። ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ።
-
15
|Juan 6:15|
በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ያነግሡት ዘንድ ሊመጡና ሊነጥቁት እንዳላቸው አውቆ ደግሞ ወደ ተራራ ብቻውን ፈቀቅ አለ።
-
16
|Juan 6:16|
በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕር ወረዱ፥
-
17
|Juan 6:17|
በታንኳም ገብተው በባሕር ማዶ ወደ ቅፍርናሆም ይመጡ ነበር። አሁንም ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር፤
-
18
|Juan 6:18|
ብርቱ ነፋስም ስለ ነፈሰ ባሕሩ ተናወጠ።
-
19
|Juan 6:19|
ሀያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ከቀዘፉ በኋላም፥ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ ታንኳይቱ ሲቀርብ አይተው ፈሩ።
-
20
|Juan 6:20|
እርሱ ግን። እኔ ነኝ፤ አትፍሩ አላቸው።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Levítico 8-10