-
-
Amharic (NT)
-
-
31
|Marcos 13:31|
ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።
-
32
|Marcos 13:32|
ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።
-
33
|Marcos 13:33|
ጊዜው መቼ እንዲሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም።
-
34
|Marcos 13:34|
ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነው፥ ለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ።
-
35
|Marcos 13:35|
እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮኽ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና
-
36
|Marcos 13:36|
ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ።
-
37
|Marcos 13:37|
ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Levítico 8-10