-
-
Amharic (NT)
-
-
1
|Marcos 5:1|
ወደ ባሕር ማዶም ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጡ።
-
2
|Marcos 5:2|
ከታንኳይቱም በወጣ ጊዜ፥ ርኵስ መንፈስ የያዘው ሰው ከመቃብር ወጥቶ ወዲያው ተገናኘው፤
-
3
|Marcos 5:3|
እርሱም በመቃብር ይኖር ነበር፥ በሰንሰለትም ስንኳ ማንም ሊያስረው በዚያን ጊዜ አይችልም ነበር፤
-
4
|Marcos 5:4|
ብዙ ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር ነበርና ዳሩ ግን ሰንሰለቱን ይበጣጥስ እግር ብረቱንም ይሰባብር ነበር፥ ሊያሸንፈውም የሚችል አልነበረም፤
-
5
|Marcos 5:5|
ሁልጊዜም ሌሊትና ቀን በመቃብርና በተራራ ሆኖ ይጮኽ ነበር ሰውነቱንም በድንጋይ ይቧጭር ነበር።
-
6
|Marcos 5:6|
ኢየሱስንም ከሩቅ ባየ ጊዜ ሮጦ ሰገደለት፥
-
7
|Marcos 5:7|
በታላቅ ድምፅም እየጮኸ። የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ አለ፤
-
8
|Marcos 5:8|
አንተ ርኵስ መንፈስ፥ ከዚህ ሰው ውጣ ብሎት ነበርና።
-
9
|Marcos 5:9|
ስምህ ማን ነው? ብሎ ጠየቀው። ብዙዎች ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው አለው፥
-
10
|Marcos 5:10|
ከአገርም ውጭ እንዳይሰዳቸው አጥብቆ ለመነው።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Levítico 8-10