-
-
Amharic (NT)
-
-
11
|Marcos 7:11|
እናንተ ግን ትላላችሁ። ሰው አባቱን ወይም እናቱን። ከእኔ የምትጠቀምበት ነገር ሁሉ ቍርባን ማለት መባ ነው ቢል፥
-
12
|Marcos 7:12|
ለአባቱና ለእናቱ ምንም እንኳ ሊያደርግ ወደ ፊት አትፈቅዱለትም፤
-
13
|Marcos 7:13|
ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።
-
14
|Marcos 7:14|
ደግሞም ሕዝቡን ጠርቶ። ሁላችሁ እኔን ስሙ አስተውሉም።
-
15
|Marcos 7:15|
ከሰው የሚወጡት ሰውን የሚያረክሱ ናቸው እንጂ ከሰው ውጭ የሚገባውስ ሊያረክሰው የሚችል ምንም የለም።
-
16
|Marcos 7:16|
የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ አላቸው።
-
17
|Marcos 7:17|
ከሕዝቡ ዘንድ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ምሳሌውን ጠየቁት።
-
18
|Marcos 7:18|
እርሱም። እናንተ ደግሞ እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሊያረክሰው ምንም እንዳይችል አትመለከቱምን?
-
19
|Marcos 7:19|
ወደ ሆድ ገብቶ ወደ እዳሪ ይወጣል እንጂ ወደ ልብ አይገባምና፤ መብልን ሁሉ እያጠራ አላቸው።
-
20
|Marcos 7:20|
እርሱም አለ። ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Levítico 8-10