-
-
Amharic (NT)
-
-
14
|Marcos 11:14|
መልሶም። ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ አላት። ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ።
-
15
|Marcos 11:15|
ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ። ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ፤
-
16
|Marcos 11:16|
ዕቃም ተሸክሞ ማንም በመቅደስ ሊያልፍ አልፈቀደም።
-
17
|Marcos 11:17|
አስተማራቸውም። ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።
-
18
|Marcos 11:18|
የካህናት አለቆችም ጻፎችም ሰምተው፥ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ይገረሙ ስለ ነበር ይፈሩት ነበርና እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ፈለጉ።
-
19
|Marcos 11:19|
ማታ ማታም ከከተማ ወደ ውጭ ይወጣ ነበር።
-
20
|Marcos 11:20|
ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት።
-
21
|Marcos 11:21|
ጴጥሮስም ትዝ ብሎት። መምህር ሆይ፥ እነሆ፥ የረገምሃት በለስ ደርቃለች አለው።
-
22
|Marcos 11:22|
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። በእግዚአብሔር እመኑ።
-
23
|Marcos 11:23|
እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ። ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 2 Corintios 5-7