-
Leer por capítulos:
-
Amharic (NT)
-
-
71
|Mateo 26:71|
ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት። ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ አለች።
-
72
|Mateo 26:72|
ዳግመኛም ሲምል። ሰውየውን አላውቀውም ብሎ ካደ።
-
73
|Mateo 26:73|
ጥቂትም ቈይተው በዚያ ቆመው የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን። አነጋገርህ ይገልጥሃልና በእውነት አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ አሉት።
-
74
|Mateo 26:74|
በዚያን ጊዜ። ሰውየውን አላውቀውም ብሎ ሊራገምና ሊምል ጀመረ። ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።
-
75
|Mateo 26:75|
ጴጥሮስም። ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ።
-
1
|Mateo 27:1|
ሲነጋም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤
-
2
|Mateo 27:2|
አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።
-
3
|Mateo 27:3|
በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ።
-
4
|Mateo 27:4|
ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን። እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ።
-
5
|Mateo 27:5|
ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 2 Corintios 5-7