-
Leer por capítulos:
-
Amharic (NT)
-
-
6
|Mateo 27:6|
የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው። የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ።
-
7
|Mateo 27:7|
ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት።
-
8
|Mateo 27:8|
ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ።
-
9
|Mateo 27:9|
በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው። ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥
-
10
|Mateo 27:10|
ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት። የሚል ተፈጸመ።
-
11
|Mateo 27:11|
ኢየሱስም በገዢው ፊት ቆመ፤ ገዢውም። የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን? ብሎ ጠየቀው፤ ኢየሱስም። አንተ አልህ አለው።
-
12
|Mateo 27:12|
የካህናት አለቆችም ሽማግሎችም ሲከሱት ምንም አልመለሰም።
-
13
|Mateo 27:13|
በዚያን ጊዜ ጲላጦስ። ስንት ያህል እንዲመሰክሩብህ አትሰማምን? አለው።
-
14
|Mateo 27:14|
ገዢውም እጅግ እስኪደነቅ ድረስ አንዲት ቃል ስንኳ አልመለሰለትም።
-
15
|Mateo 27:15|
በዚያም በዓል ሕዝቡ የወደዱትን አንድ እስረኛ ሊፈታላቸው ለገዢው ልማድ ነበረው።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 17-19