-
Leia por capÃtulos
-
Amharic (NT) -
-
1
|Mateus 15:1|
በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና።
-
2
|Mateus 15:2|
ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና አሉት።
-
3
|Mateus 15:3|
እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው። እናንተስ ስለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ምን ትተላለፋላችሁ?
-
4
|Mateus 15:4|
እግዚአብሔር። አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ። አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና፤
-
5
|Mateus 15:5|
እናንተ ግን። አባቱን ወይም እናቱን። ከእኔ የምትጠቀምበት መባ ነው የሚል ሁሉ፥
-
6
|Mateus 15:6|
አባቱን ወይም እናቱን አያከብርም ትላላችሁ፤ ስለ ወጋችሁም የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ።
-
7
|Mateus 15:7|
እናንተ ግብዞች፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ።
-
8
|Mateus 15:8|
ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤
-
9
|Mateus 15:9|
የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
-
10
|Mateus 15:10|
ሕዝቡንም ጠርቶ። ስሙ አስተውሉም፤
-
-
Sugestões

Clique para ler Apocalipse 21-21