-
Leia por capÃtulos
-
Amharic (NT) -
-
1
|Mateus 26:1|
ኢየሱስም እነዚህን ቃሎች ሁሉ በፈጸመ ጊዜ፥
-
2
|Mateus 26:2|
ለደቀ መዛሙርቱ። ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንዲሆን ታውቃላችሁ፥ የሰው ልጅም ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል አለ።
-
3
|Mateus 26:3|
በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥
-
4
|Mateus 26:4|
ኢየሱስንም በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉትም ተማከሩ፤
-
5
|Mateus 26:5|
ነገር ግን። በሕዝቡ ዘንድ ሁከት እንዳይነሣ በበዓል አይሁን አሉ።
-
6
|Mateus 26:6|
ኢየሱስም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ፥
-
7
|Mateus 26:7|
አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።
-
8
|Mateus 26:8|
ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቈጡና። ይህ ጥፋት ለምንድር ነው?
-
9
|Mateus 26:9|
ይህ በብዙ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና አሉ።
-
10
|Mateus 26:10|
ኢየሱስም ይህን አውቆ እንዲህ አላቸው። መልካም ሥራ ሠርታልኛለችና ሴቲቱንስ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ?
-
-
Sugestões

Clique para ler Apocalipse 21-21