-
Leia por capÃtulos
-
Amharic (NT) -
-
21
|Mateus 9:21|
በልብዋ። ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ ትል ነበረችና።
-
22
|Mateus 9:22|
ኢየሱስም ዘወር ብሎ አያትና። ልጄ ሆይ፥ አይዞሽ፤ እምነትሽ አድኖሻል አላት። ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምራ ዳነች።
-
23
|Mateus 9:23|
ኢየሱስም ወደ መኰንኑ ቤት በደረሰ ጊዜ፥ እምቢልተኞችንና የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ።
-
24
|Mateus 9:24|
ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ አላቸው። በጣምም ሳቁበት።
-
25
|Mateus 9:25|
ሕዝቡን ግን ከአስወጡ በኋላ ገብቶ እጅዋን ያዛት፥ ብላቴናይቱም ተነሣች።
-
26
|Mateus 9:26|
ያም ዝና ወደዚያ አገር ሁሉ ወጣ።
-
27
|Mateus 9:27|
ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች። የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረን ብለው እየጮሁ ተከተሉት።
-
28
|Mateus 9:28|
ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፥ ኢየሱስም። ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን? አላቸው። አዎን፥ ጌታ ሆይ አሉት።
-
29
|Mateus 9:29|
በዚያን ጊዜ። እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ ብሎ ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ።
-
30
|Mateus 9:30|
ዓይኖቻቸውም ተከፈቱ።
-
-
Sugestões

Clique para ler Apocalipse 21-21