-
-
Amharic (NT)
-
-
1
|Lucas 14:1|
በሰንበትም ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት እንጀራ ሊበላ በገባ ጊዜ እነርሱ ይጠባበቁት ነበር።
-
2
|Lucas 14:2|
እነሆም፥ ሆዱ የተነፋ ሰው በፊቱ ነበረ።
-
3
|Lucas 14:3|
ኢየሱስም መልሶ። በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? ብሎ ለሕግ አዋቂዎችና ለፈሪሳውያን ተናገረ።
-
4
|Lucas 14:4|
እነርሱ ግን ዝም አሉ። ይዞም ፈወሰውና አሰናበተው።
-
5
|Lucas 14:5|
ከእናንተ አህያው ወይስ በሬው በጕድጓድ ቢወድቅ በሰንበት ወዲያው የማያወጣው ማን ነው? አላቸው።
-
6
|Lucas 14:6|
ስለዚህ ነገርም ሊመልሱለት አልተቻላቸውም።
-
7
|Lucas 14:7|
የታደሙትንም የከበሬታ ስፍራ እንደ መረጡ ተመልክቶ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህ ሲል።
-
8
|Lucas 14:8|
ማንም ለሰርግ ቢጠራህ በከበሬታ ስፍራ አትቀመጥ፤ ምናልባት ከአንተ ይልቅ የከበረ ተጠርቶ ይሆናልና አንተን እርሱንም የጠራ መጥቶ።
-
9
|Lucas 14:9|
ለዚህ ስፍራ ተውለት ይልሃል፥ በዚያን ጊዜም እያፈርህ በዝቅተኛው ስፍራ ልትሆን ትጀምራለህ።
-
10
|Lucas 14:10|
ነገር ግን በተጠራህ ጊዜ፥ የጠራህ መጥቶ። ወዳጄ ሆይ፥ ወደ ላይ ውጣ እንዲልህ፥ ሄደህ በዝቅተኛው ስፍራ ተቀመጥ፤ ያን ጊዜም ከአንተ ጋር በተቀመጡት ሁሉ ፊት ክብር ይሆንልሃል።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 2 Corintios 5-7