-
-
Amharic (NT)
-
-
1
|Lucas 22:1|
ፋሲካም የሚባለው የቂጣ በዓል ቀረበ።
-
2
|Lucas 22:2|
የካህናት አለቆችና ጻፎችም እንዴት እንዲያጠፉት ይፈልጉ ነበር፤ ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።
-
3
|Lucas 22:3|
ሰይጣንም ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው የአስቆሮቱ በሚባለው በይሁዳ ገባ፤
-
4
|Lucas 22:4|
ሄዶም እንዴት አሳልፎ እንዲሰጣቸው ከካህናት አለቆችና ከመቅደስ አዛዦች ጋር ተነጋገረ።
-
5
|Lucas 22:5|
እነርሱም ደስ አላቸው፥ ገንዘብም ሊሰጡት ተዋዋሉ።
-
6
|Lucas 22:6|
እሺም አለ፥ ሕዝብም በሌለበት አሳልፎ እንዲሰጣቸው ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር።
-
7
|Lucas 22:7|
ፋሲካንም ሊያርዱበት የሚገባው የቂጣ በዓል ደረሰ፤
-
8
|Lucas 22:8|
ጴጥሮስንና ዮሐንስንም። ፋሲካን እንድንበላ ሄዳችሁ አዘጋጁልን ብሎ ላካቸው።
-
9
|Lucas 22:9|
እነርሱም። ወዴት እናዘጋጅ ዘንድ ትወዳለህ? አሉት።
-
10
|Lucas 22:10|
እርሱም አላቸው። እነሆ፥ ወደ ከተማ ስትገቡ ማድጋ ውኃ የተሸከመ ሰው ይገናኛችኋል፤ ወደ ሚገባበት ቤት ተከተሉት፤
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Levítico 8-10