-
-
Amharic (NT)
-
-
62
|Lucas 22:62|
ጴጥሮስም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ።
-
63
|Lucas 22:63|
ኢየሱስንም የያዙት ሰዎች ይዘብቱበትና ይደበድቡት ነበር፤
-
64
|Lucas 22:64|
ሸፍነውም ፊቱን ይመቱት ነበርና። በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገር እያሉ ይጠይቁት ነበር።
-
65
|Lucas 22:65|
ሌላም ብዙ ነገር እየተሳደቡ በእርሱ ላይ ይናገሩ ነበር።
-
66
|Lucas 22:66|
በነጋም ጊዜ የሕዝቡ ሽማግሌዎችና የካህናት አለቆች ጻፎችም ተሰብስበው ወደ ሸንጎአቸው ወሰዱትና
-
67
|Lucas 22:67|
ክርስቶስ አንተ ነህን? ንገረን አሉት። እርሱ ግን እንዲህ አላቸው። ብነግራችሁ አታምኑም፤
-
68
|Lucas 22:68|
ብጠይቅም አትመልሱልኝም አትፈቱኝምም።
-
69
|Lucas 22:69|
ነገር ግን ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ኃይል ቀኝ ይቀመጣል።
-
70
|Lucas 22:70|
ሁላቸውም። እንግዲያስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህን? አሉት። እርሱም። እኔ እንደ ሆንሁ እናንተ ትላላችሁ አላቸው።
-
71
|Lucas 22:71|
እነርሱም። ራሳችን ከአፉ ሰምተናልና ከእንግዲህ ወዲህ ምን ምስክር ያስፈልገናል? አሉ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Levítico 8-10