-
-
Amharic (NT)
-
-
32
|Lucas 19:32|
የተላኩትም ሄደው እንዳላቸው አገኙ።
-
33
|Lucas 19:33|
እነርሱም ውርንጫውን ሲፈቱ ጌቶቹ። ውርንጫውን ስለ ምን ትፈቱታላችሁ? አሉአቸውም
-
34
|Lucas 19:34|
እነርሱም። ለጌታ ያስፈልገዋል አሉ።
-
35
|Lucas 19:35|
ወደ ኢየሱስም አመጡት፥ በውርንጫውም ላይ ልብሳቸውን ጭነው ኢየሱስን አስቀመጡት።
-
36
|Lucas 19:36|
ሲሄድም ልብሳቸውን በመንገድ ያነጥፉ ነበር።
-
37
|Lucas 19:37|
ወደ ደብረ ዘይት ቍልቍለትም አሁን በቀረበ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ሁላቸው ደስ እያላቸው ተአምራትን ሁሉ ስላዩ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ጀምረው።
-
38
|Lucas 19:38|
በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያምም ክብር አሉ።
-
39
|Lucas 19:39|
ከሕዝብም መካከል ከፈሪሳውያን አንዳንዱ። መምህር ሆይ፥ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው አሉት።
-
40
|Lucas 19:40|
መልሶም። እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ አላቸው።
-
41
|Lucas 19:41|
ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት፥
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Levítico 8-10