-
-
Amharic (NT)
-
-
11
|Lucas 21:11|
ታላቅም የምድር መናወጥና በልዩ ልዩ ስፍራ ቸነፈር ራብም ይሆናል፤ የሚያስፈራም ነገር ከሰማይም ታላቅ ምልክት ይሆናል።
-
12
|Lucas 21:12|
ከዚህም ሁሉ በፊት እጃቸውን በላያችሁ ይጭናሉ ያሳድዱአችሁማል፤ ስለ ስሜም ወደ ምኵራብና ወደ ወኅኒ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎችም ይወስዱአችኋል፤
-
13
|Lucas 21:13|
ይህም ለምስክርነት ይሆንላችኋል።
-
14
|Lucas 21:14|
ሰለዚህ እንዴት እንድትመልሱ አስቀድማችሁ እንዳታስቡ በልባችሁ አኑሩት፤
-
15
|Lucas 21:15|
ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።
-
16
|Lucas 21:16|
ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ፤
-
17
|Lucas 21:17|
በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።
-
18
|Lucas 21:18|
ከራሳችሁም አንዲት ጠጉር ስንኳ አትጠፋም፤
-
19
|Lucas 21:19|
በመታገሣችሁም ነፍሳችሁን ታገኛላችሁ።
-
20
|Lucas 21:20|
ኢየሩሳሌም ግን በጭፍራ ተከባ ስታዩ በዚያን ጊዜ ጥፋትዋ እንደ ቀረበ እወቁ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Levítico 11-12