-
-
Amharic (NT)
-
-
44
|Lucas 24:44|
እርሱም። ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው።
-
45
|Lucas 24:45|
በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤
-
46
|Lucas 24:46|
እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥
-
47
|Lucas 24:47|
በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።
-
48
|Lucas 24:48|
እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ።
-
49
|Lucas 24:49|
እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ።
-
50
|Lucas 24:50|
እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።
-
51
|Lucas 24:51|
ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።
-
52
|Lucas 24:52|
እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥
-
53
|Lucas 24:53|
ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 17-19