-
-
Amharic (NT)
-
-
11
|Marcos 11:11|
ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባ፤ ዘወር ብሎም ሁሉን ከተመለከተ በኋላ፥ ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ ከአሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ።
-
12
|Marcos 11:12|
በማግሥቱም ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ።
-
13
|Marcos 11:13|
ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ፥ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም።
-
14
|Marcos 11:14|
መልሶም። ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ አላት። ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ።
-
15
|Marcos 11:15|
ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ። ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ፤
-
16
|Marcos 11:16|
ዕቃም ተሸክሞ ማንም በመቅደስ ሊያልፍ አልፈቀደም።
-
17
|Marcos 11:17|
አስተማራቸውም። ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።
-
18
|Marcos 11:18|
የካህናት አለቆችም ጻፎችም ሰምተው፥ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ይገረሙ ስለ ነበር ይፈሩት ነበርና እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ፈለጉ።
-
19
|Marcos 11:19|
ማታ ማታም ከከተማ ወደ ውጭ ይወጣ ነበር።
-
20
|Marcos 11:20|
ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Levítico 8-10