-
-
Amharic (NT)
-
-
33
|Marcos 1:33|
ከተማይቱም ሁላ በደጅ ተሰብስባ ነበር።
-
34
|Marcos 1:34|
በልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፥ ብዙዎችንም አጋንንት አወጣ፥ አጋንንትም ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና ሊናገሩ አልፈቀደላቸውም።
-
35
|Marcos 1:35|
ማለዳም ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ።
-
36
|Marcos 1:36|
ስምዖንና ከእርሱ ጋር የነበሩትም ገሥግሠው ተከተሉት፥
-
37
|Marcos 1:37|
ባገኙትም ጊዜ። ሁሉ ይፈልጉሃል አሉት።
-
38
|Marcos 1:38|
እርሱም። በዚያ ደግሞ ልሰብክ ወደ ሌላ ስፍራ በቅርብ ወዳሉ መንደሮች እንሂድ ስለዚህ ወጥቻለሁና አላቸው።
-
39
|Marcos 1:39|
በምኵራባቸውም እየሰበከ አጋንንትንም እያወጣ ወደ ገሊላ ሁሉ መጣ።
-
40
|Marcos 1:40|
ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና። ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው።
-
41
|Marcos 1:41|
ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና። እወድዳለሁ፤ ንጻ አለው።
-
42
|Marcos 1:42|
በተናገረም ጊዜ ለምጹ ወዲያው ለቀቀውና ነጻ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Gálatas 1-3