-
-
Amharic (NT)
-
-
11
|Marcos 3:11|
ርኵሳን መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ተደፍተው። አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉ ጮኹ።
-
12
|Marcos 3:12|
እንዳይገልጡትም በጣም አዘዛቸው።
-
13
|Marcos 3:13|
ወደ ተራራም ወጣ፥ ራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ፥ ወደ እርሱም ሄዱ።
-
14
|Marcos 3:14|
ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው፥
-
15
|Marcos 3:15|
ድውዮችንም ሊፈውሱ አጋንንትንም ሊያወጡ ሥልጣን ይሆንላቸው ዘንድ አሥራ ሁለት አደረገ፤
-
16
|Marcos 3:16|
ስምዖንንም ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው፤
-
17
|Marcos 3:17|
የዘብዴዎስንም ልጅ ያዕቆብን የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፥ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤
-
18
|Marcos 3:18|
እንድርያስንም ፊልጶስንም በርተሎሜውስንም ማቴዎስንም ቶማስንም የእልፍዮስን ልጅ ያዕቆብንም ታዴዎስንም ቀነናዊውንም ስምዖንን፥
-
19
|Marcos 3:19|
አሳልፎ የሰጠውንም የአስቆሮቱን ይሁዳን።
-
20
|Marcos 3:20|
ወደ ቤትም መጡ፤ እንጀራም መብላት ስንኳ እስኪሳናቸው ድረስ እንደ ገና ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 17-19