-
-
Amharic (NT)
-
-
21
|Marcos 3:21|
ዘመዶቹም ሰምተው። አበደ ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።
-
22
|Marcos 3:22|
ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም። ብዔል ዜቡል አለበት፤ ደግሞ። በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል ብለው ተናገሩ።
-
23
|Marcos 3:23|
እነርሱንም ወደ እርሱ ጠርቶ በምሳሌ አላቸው። ሰይጣን ሰይጣንን ሊያወጣው እንዴት ይችላል?
-
24
|Marcos 3:24|
መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤
-
25
|Marcos 3:25|
ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ያ ቤት ሊቆም አይችልም።
-
26
|Marcos 3:26|
ሰይጣንም ራሱን ተቃውሞ ከተለያየ፥ መጨረሻ ይሆንበታል እንጂ ሊቆም አይችልም።
-
27
|Marcos 3:27|
ነገር ግን አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም፥ ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።
-
28
|Marcos 3:28|
እውነት እላችኋለሁ፥ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤
-
29
|Marcos 3:29|
በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኃጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም።
-
30
|Marcos 3:30|
ርኵስ መንፈስ አለበት ይሉ ነበርና።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 1 Corintios 8-10