-
-
Amharic (NT)
-
-
11
|Marcos 15:11|
የካህናት አለቆች ግን በርባንን በእርሱ ፈንታ ይፈታላቸው ዘንድ ሕዝቡን አወኩአቸው።
-
12
|Marcos 15:12|
ጲላጦስም ዳግመኛ መልሶ። እንግዲህ የአይሁድ ንጉሥ የምትሉትን ምን ላደርገው ትወዳላችሁ? አላቸው።
-
13
|Marcos 15:13|
እነርሱም ዳግመኛ። ስቀለው እያሉ ጮኹ።
-
14
|Marcos 15:14|
ጲላጦስም። ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱ ግን። ስቀለው እያሉ ጩኸት አበዙ።
-
15
|Marcos 15:15|
ጲላጦስም የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ።
-
16
|Marcos 15:16|
ወታደሮችም ፕራይቶሪዮን ወደሚባል ግቢ ውስጥ ወሰዱት፥ ጭፍራውንም ሁሉ በአንድነት ጠሩ።
-
17
|Marcos 15:17|
ቀይ ልብስም አለበሱት፥ የእሾህ አክሊልም ጎንጉነው ደፉበት፤
-
18
|Marcos 15:18|
የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ እጅ ይነሱት ጀመር፤
-
19
|Marcos 15:19|
ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት።
-
20
|Marcos 15:20|
ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት፥ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 1 Corintios 8-10