-
-
Amharic (NT)
-
-
21
|Marcos 15:21|
አንድ መንገድ አላፊም የአሌክስንድሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።
-
22
|Marcos 15:22|
ትርጓሜውም የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ ወሰዱት።
-
23
|Marcos 15:23|
ከርቤም የተቀላቀለበትን የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤ እርሱ ግን አልተቀበለም።
-
24
|Marcos 15:24|
ሰቀሉትም፥ ልብሱንም ማን ማን እንዲወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉ።
-
25
|Marcos 15:25|
በሰቀሉትም ጊዜ ሦስት ሰዓት ነበረ።
-
26
|Marcos 15:26|
የክሱ ጽሕፈትም። የአይሁድ ንጉሥ የሚል ተጽፎ ነበር።
-
27
|Marcos 15:27|
ከእርሱም ጋር ሁለት ወንበዶች አንዱን በቀኙ አንዱንም በግራው ሰቀሉ።
-
28
|Marcos 15:28|
መጽሐፍም። ከአመፀኞች ጋር ተቆጠረ ያለው ተፈጸመ።
-
29
|Marcos 15:29|
የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና። ዋ፥ ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራ፥
-
30
|Marcos 15:30|
ከመስቀል ወርደህ ራስህን አድን አሉ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 17-19