-
-
Amharic (NT)
-
-
35
|Lucas 24:35|
እነርሱም በመንገድ የሆነውን እንጀራውንም በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንደ ታወቀላቸው ተረኩላቸው።
-
36
|Lucas 24:36|
ይህንም ሲነጋገሩ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።
-
37
|Lucas 24:37|
ነገር ግን ደነገጡና ፈሩ መንፈስም ያዩ መሰላቸው።
-
38
|Lucas 24:38|
እርሱም። ስለ ምን ትደነግጣላችሁ? ስለ ምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል?
-
39
|Lucas 24:39|
እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው።
-
40
|Lucas 24:40|
ይህንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው።
-
41
|Lucas 24:41|
እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ። በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን? አላቸው።
-
42
|Lucas 24:42|
እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፥ ከማር ወለላም ሰጡት፤
-
43
|Lucas 24:43|
ተቀብሎም በፊታቸው በላ።
-
44
|Lucas 24:44|
እርሱም። ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 17-19