-
-
Amharic (NT)
-
-
16
|Lucas 23:16|
እንግዲያስ ቀጥቼ እፈታዋለሁ። በበዓሉ አንድ ይፈታላቸው ዘንድ ግድ ነበረና።
-
18
|Lucas 23:18|
ሁላቸውም በአንድነት። ይህን አስወግድ፥ በርባንንም ፍታልን እያሉ ጮኹ፤
-
19
|Lucas 23:19|
እርሱም ሁከትን በከተማ አንሥቶ ሰውን ስለ ገደለ በወኅኒ ታስሮ ነበር።
-
20
|Lucas 23:20|
ጲላጦስም ኢየሱስን ሊፈታ ወድዶ ዳግመኛ ተናገራቸው፤
-
21
|Lucas 23:21|
ነገር ግን እነርሱ። ስቀለው ስቀለው እያሉ ይጮኹ ነበር።
-
22
|Lucas 23:22|
ሦስተኛም። ምን ነው? ያደረገውስ ክፋት ምንድር ነው? ለሞት የሚያደርሰው በደል አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ቀጥቼ እፈታዋለሁ አላቸው።
-
23
|Lucas 23:23|
እነርሱ ግን እንዲሰቀል በታላቅ ድምፅ አጽንተው ለመኑት። የእነርሱ ጩኸትና የካህናት አለቆችም ቃል በረታ።
-
24
|Lucas 23:24|
ጲላጦስም ልመናቸው እንዲሆንላቸው ፈረደበት።
-
25
|Lucas 23:25|
ያንን የለመኑትንም፥ ስለ ሁከት ሰውንም ስለ መግደል በወኅኒ ታስሮ የነበረውን አስፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው።
-
26
|Lucas 23:26|
በወሰዱትም ጊዜ ስምዖን የተባለ የቀሬናን ሰው ከገጠር ሲመጣ ይዘው ከኢየሱስ በኋላ መስቀሉን እንዲሸከም ጫኑበት።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 2 Reyes 6-8