-
-
Amharic (NT)
-
-
67
|Lucas 22:67|
ክርስቶስ አንተ ነህን? ንገረን አሉት። እርሱ ግን እንዲህ አላቸው። ብነግራችሁ አታምኑም፤
-
68
|Lucas 22:68|
ብጠይቅም አትመልሱልኝም አትፈቱኝምም።
-
69
|Lucas 22:69|
ነገር ግን ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ኃይል ቀኝ ይቀመጣል።
-
70
|Lucas 22:70|
ሁላቸውም። እንግዲያስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህን? አሉት። እርሱም። እኔ እንደ ሆንሁ እናንተ ትላላችሁ አላቸው።
-
71
|Lucas 22:71|
እነርሱም። ራሳችን ከአፉ ሰምተናልና ከእንግዲህ ወዲህ ምን ምስክር ያስፈልገናል? አሉ።
-
1
|Lucas 23:1|
ሁሉም በሞላው ተነሥተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱትና።
-
2
|Lucas 23:2|
ይህ ሕዝባችንን ሲያጣምም ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል ደግሞም። እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ ሲል አገኘነው ብለው ይከሱት ጀመር።
-
3
|Lucas 23:3|
ጲላጦስም። አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን? ብሎ ጠየቀው። እርሱም መልሶ። አንተ አልህ አለው።
-
4
|Lucas 23:4|
ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ። በዚህ ሰው አንድ በደል ስንኳ አላገኘሁበትም አለ።
-
5
|Lucas 23:5|
እነርሱ ግን አጽንተው። ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ በይሁዳ ሁሉ እያስተማረ ሕዝቡን ያውካል አሉ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 28-30