-
-
Amharic (NT)
-
-
57
|Lucas 22:57|
እርሱ ግን። አንቺ ሴት፥ አላውቀውም ብሎ ካደ።
-
58
|Lucas 22:58|
ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሌላው አይቶት። አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ አለው። ጴጥሮስ ግን። አንተ ሰው፥ እኔ አይደለሁም አለ።
-
59
|Lucas 22:59|
አንድ ሰዓትም የሚያህል ቆይቶ ሌላው አስረግጦ። እርሱ የገሊላ ሰው ነውና በእውነት ይህ ደግሞ ከእርሱ ጋር ነበረ አለ።
-
60
|Lucas 22:60|
ጴጥሮስ ግን። አንተ ሰው፥ የምትለውን አላውቅም አለ። ያን ጊዜም ገና ሲናገር ዶሮ ጮኸ።
-
61
|Lucas 22:61|
ጌታም ዘወር ብሎ ጴጥሮስን ተመለከተው፤ ጴጥሮስም። ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ እንዳለው የጌታ ቃል ትዝ አለው።
-
62
|Lucas 22:62|
ጴጥሮስም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ።
-
63
|Lucas 22:63|
ኢየሱስንም የያዙት ሰዎች ይዘብቱበትና ይደበድቡት ነበር፤
-
64
|Lucas 22:64|
ሸፍነውም ፊቱን ይመቱት ነበርና። በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገር እያሉ ይጠይቁት ነበር።
-
65
|Lucas 22:65|
ሌላም ብዙ ነገር እየተሳደቡ በእርሱ ላይ ይናገሩ ነበር።
-
66
|Lucas 22:66|
በነጋም ጊዜ የሕዝቡ ሽማግሌዎችና የካህናት አለቆች ጻፎችም ተሰብስበው ወደ ሸንጎአቸው ወሰዱትና
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 2 Reyes 6-8