- 
			
				
- 
									
   Amharic (NT)									 - 
									
									 
- 
									
									13
									 
									 
									|Santiago 4:13|
									አሁንም። ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና።									
									    
								 
- 
									
									14
									 
									 
									|Santiago 4:14|
									ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና።									
									    
								 
- 
									
									15
									 
									 
									|Santiago 4:15|
									በዚህ ፈንታ። ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።									
									    
								 
- 
									
									16
									 
									 
									|Santiago 4:16|
									አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንደዚህ ያለ ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው።									
									    
								 
- 
									
									17
									 
									 
									|Santiago 4:17|
									እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው።									
									    
								 
- 
									
									1
									 
									 
									|Santiago 5:1|
									አሁንም እናንተ ባለ ጠጎች፥ ስለሚደርስባችሁ ጭንቅ ዋይ ዋይ እያላችሁ አልቅሱ።									
									    
								 
- 
									
									2
									 
									 
									|Santiago 5:2|
									ሀብታችሁ ተበላሽቶአል፥ ልብሳችሁም በብል ተበልቶአል።									
									    
								 
- 
									
									3
									 
									 
									|Santiago 5:3|
									ወርቃችሁም ብራችሁም ዝጎአል፥ ዝገቱም ምስክር ይሆንባችኋል ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላል። ለኋለኛው ቀን መዝገብን አከማችታችኋል።									
									    
								 
- 
									
									4
									 
									 
									|Santiago 5:4|
									እነሆ፥ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፥ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ፀባዖት ጆሮ ገብቶአል።									
									    
								 
- 
									
									5
									 
									 
									|Santiago 5:5|
									በምድር ላይ ተቀማጥላችኋል በሴሰኝነትም ኖራችኋል፤ ለእርድ ቀን እንደሚያወፍር ልባችሁን አወፍራችኋል።									
									    
								 
 - 
									
 - 
				
Sugerencias
 

Haga clic para leer Juan 16-18