-
-
Amharic (NT)
-
-
1
|1 Corintios 11:1|
እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።
-
2
|1 Corintios 11:2|
ወንድሞች ሆይ፥ በሁሉ ስለምታስቡኝና አሳልፌ እንደ ሰጠኋችሁ ወግን ፈጽማችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።
-
3
|1 Corintios 11:3|
ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ።
-
4
|1 Corintios 11:4|
ራሱን ተከናንቦ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ወንድ ሁሉ ራሱን ያዋርዳል።
-
5
|1 Corintios 11:5|
ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል አንድ ነውና።
-
6
|1 Corintios 11:6|
ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።
-
7
|1 Corintios 11:7|
ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌና ክብር ስለ ሆነ ራሱን መከናነብ አይገባውም፤ ሴት ግን የወንድ ክብር ናት።
-
8
|1 Corintios 11:8|
ሴት ከወንድ ናት እንጂ ወንድ ከሴት አይደለምና።
-
9
|1 Corintios 11:9|
ሴት ስለ ወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ስለ ሴት አልተፈጠረምና።
-
10
|1 Corintios 11:10|
ስለዚህ ሴት ከመላእክት የተነሣ በራስዋ ሥልጣን ሊኖራት ይገባል።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 25-27