- 
			
				
- 
									
   Amharic (NT)									 - 
									
									 
- 
									
									1
									 
									 
									|1 Corintios 14:1|
									ፍቅርን ተከታተሉ፥ መንፈሳዊ ስጦታንም ይልቁንም ትንቢት መናገርን በብርቱ ፈልጉ።									
									    
								 
- 
									
									2
									 
									 
									|1 Corintios 14:2|
									በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤									
									    
								 
- 
									
									3
									 
									 
									|1 Corintios 14:3|
									ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽና ለመምከር ለማጽናናትም ለሰው ይናገራል።									
									    
								 
- 
									
									4
									 
									 
									|1 Corintios 14:4|
									በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል።									
									    
								 
- 
									
									5
									 
									 
									|1 Corintios 14:5|
									ሁላችሁ በልሳኖች ልትናገሩ እወድ ነበር፥ ትንቢትን ልትናገሩ ግን ከዚህ ይልቅ እወዳለሁ፤ ማኅበሩ ይታነጽ ዘንድ ንግግሩን ባይተረጐም በልሳኖች ከሚናገር ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል።									
									    
								 
- 
									
									6
									 
									 
									|1 Corintios 14:6|
									አሁን ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ መጥቼ በልሳኖች ብናገር፥ በመግለጥ ወይም በእውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኋችሁ ምን እጠቅማችኋለሁ?									
									    
								 
- 
									
									7
									 
									 
									|1 Corintios 14:7|
									ነፍስ የሌለበት ነገር እንኳ ዋሽንትም ክራርም ቢሆን ድምፅ ሲሰጥ የድምፁን ልዩነት ባይገልጥ በዋሽንት የሚነፋው ወይስ በክራር የሚመታው መዝሙር እንዴት ይታወቃል?									
									    
								 
- 
									
									8
									 
									 
									|1 Corintios 14:8|
									ደግሞም መለከት የማይገለጥን ድምፅ ቢሰጥ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል?									
									    
								 
- 
									
									9
									 
									 
									|1 Corintios 14:9|
									እንዲሁ እናንተ ደግሞ የተገለጠውን ቃል በአንደበት ባትናገሩ ሰዎች የምትናገሩትን እንዴት አድርገው ያስተውሉታል? ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁና።									
									    
								 
- 
									
									10
									 
									 
									|1 Corintios 14:10|
									በዓለም ምናልባት ቁጥር የሌለው የቋንቋ ዓይነት ይኖራል ቋንቋም የሌለው ሕዝብ የለም፤									
									    
								 
 - 
									
 - 
				
Sugerencias
 

Haga clic para leer Juan 16-18