-
-
Amharic (NT)
-
-
31
|1 Corintios 14:31|
ሁሉም እንዲማሩ ሁሉም እንዲመከሩ ሁላችሁ በእያንዳንዳችሁ ትንቢት ልትናገሩ ትችላላችሁ።
-
32
|1 Corintios 14:32|
የነቢያትም መናፍስት ለነቢያት ይገዛሉ፤
-
33
|1 Corintios 14:33|
እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው።
-
34
|1 Corintios 14:34|
ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ፤ ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና።
-
35
|1 Corintios 14:35|
ለሴት በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነውና፥ ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ።
-
36
|1 Corintios 14:36|
ምን ነው? የእግዚአብሔር ቃል የወጣ ከእናንተ ነውን? ወይስ ወደ እናንተ ብቻ ደርሶአልን?
-
37
|1 Corintios 14:37|
ማንም ነቢይ ወይም መንፈሳዊ የሆነ ቢመስለው ይህች የጻፍሁላችሁ የጌታ ትእዛዝ እንደ ሆነች ይወቅ፤
-
38
|1 Corintios 14:38|
ማንም የማያውቅ ቢኖር ግን አይወቅ።
-
39
|1 Corintios 14:39|
ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፥ በልሳኖች ከመናገርም አትከልክሉ፤
-
40
|1 Corintios 14:40|
ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Gálatas 1-3