-
-
Amharic (NT)
-
-
11
|1 Corintios 14:11|
እንግዲህ የቋንቋውን ፍች ባላውቅ ለሚናገረው እንግዳ እሆናለሁ፥ የሚናገረውም ለእኔ እንግዳ ይሆናል።
-
12
|1 Corintios 14:12|
እንዲሁ ደግሞ እናንተ መንፈሳዊ ስጦታን በብርቱ የምትፈልጉ ከሆናችሁ ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ እንዲበዛላችሁ ፈልጉ።
-
13
|1 Corintios 14:13|
ስለዚህ በልሳን የሚናገር እንዲተረጉም ይጸልይ።
-
14
|1 Corintios 14:14|
በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።
-
15
|1 Corintios 14:15|
እንግዲህ ምንድር ነው? በመንፈስ እጸልያለሁ በአእምሮም ደግሞ እጸልያለሁ፤ በመንፈስ እዘምራለሁ በአእምሮም ደግሞ እዘምራለሁ።
-
16
|1 Corintios 14:16|
እንዲያማ ካልሆነ፥ አንተ በመንፈስ ብትባርክ ባልተማሩት ስፍራ የተቀመጠው የምትለውን ካላወቀ እንዴት አድርጎ ለምስጋናህ አሜን ይላል?
-
17
|1 Corintios 14:17|
አንተማ መልካም ታመሰግናለህ፥ ሌላው ግን አይታነጽበትም።
-
18
|1 Corintios 14:18|
ከሁላችሁ ይልቅ በልሳኖች እናገራለሁና እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤
-
19
|1 Corintios 14:19|
ነገር ግን ሌሎችን ደግሞ አስተምር ዘንድ በማኅበር እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ።
-
20
|1 Corintios 14:20|
ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 2 Reyes 6-8