- 
			
				
- 
									
   Amharic (NT)									 - 
									
									 
- 
									
									1
									 
									 
									|1 Corintios 12:1|
									ስለ መንፈሳዊ ነገርም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።									
									    
								 
- 
									
									2
									 
									 
									|1 Corintios 12:2|
									አሕዛብ ሳላችሁ በማናቸውም ጊዜ እንደምትመሩ ድምፅ ወደሌላቸው ወደ ጣዖታት እንደ ተወሰዳችሁ ታውቃላችሁ።									
									    
								 
- 
									
									3
									 
									 
									|1 Corintios 12:3|
									ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር። ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር። ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።									
									    
								 
- 
									
									4
									 
									 
									|1 Corintios 12:4|
									የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤									
									    
								 
- 
									
									5
									 
									 
									|1 Corintios 12:5|
									አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤									
									    
								 
- 
									
									6
									 
									 
									|1 Corintios 12:6|
									አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።									
									    
								 
- 
									
									7
									 
									 
									|1 Corintios 12:7|
									ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል።									
									    
								 
- 
									
									8
									 
									 
									|1 Corintios 12:8|
									ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፥									
									    
								 
- 
									
									9
									 
									 
									|1 Corintios 12:9|
									ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ፥ ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥									
									    
								 
- 
									
									10
									 
									 
									|1 Corintios 12:10|
									ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤									
									    
								 
 - 
									
 - 
				
Sugerencias
 

Haga clic para leer Juan 16-18