-
-
Amharic (NT)
-
-
11
|1 Corintios 4:11|
እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፥ እንጠማለን፥ እንራቆታለን፥ እንጐሰማለን፥ እንንከራተታለን፥
-
12
|1 Corintios 4:12|
በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲሰድቡን እንመርቃለን፥ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፥ ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን፤
-
13
|1 Corintios 4:13|
እስከ አሁን ድረስ የዓለም ጥራጊ የሁሉም ጉድፍ ሆነናል።
-
14
|1 Corintios 4:14|
እንደምወዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልገሥጻችሁ እንጂ ላሳፍራችሁ ይህን አልጽፍም።
-
15
|1 Corintios 4:15|
በክርስቶስ አእላፍ ሞግዚቶች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ወልጄአችኋለሁና።
-
16
|1 Corintios 4:16|
እንግዲህ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።
-
17
|1 Corintios 4:17|
ስለዚህ የምወደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፥ እኔም በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንደማስተምር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚሆነውን መንገዴን እርሱ ያሳስባችኋል።
-
18
|1 Corintios 4:18|
አንዳንዱ ግን ወደ እናንተ የማልመጣ እየመሰላቸው የታበዩ አሉ፤
-
19
|1 Corintios 4:19|
ነገር ግን ጌታ ቢፈቅድ ፈጥኜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፥ የትዕቢተኞችንም ኃይል አውቃለሁ እንጂ ቃላቸውን አይደለም፤
-
20
|1 Corintios 4:20|
የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ነው እንጂ በቃል አይደለምና።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 28-30