-
-
Amharic (NT)
-
-
11
|1 Corintios 12:11|
ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።
-
12
|1 Corintios 12:12|
አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤
-
13
|1 Corintios 12:13|
አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።
-
14
|1 Corintios 12:14|
አካል ብዙ ብልቶች እንጂ አንድ ብልት አይደለምና።
-
15
|1 Corintios 12:15|
እግር። እኔ እጅ አይደለሁምና የአካል ክፍል አይደለሁም ብትል፥ ይህን በማለትዋ የአካል ክፍል መሆንዋ ይቀራልን?
-
16
|1 Corintios 12:16|
ጆሮም። እኔ ዓይን አይደለሁምና የአካል ክፍል አይደለሁም ቢል፥ ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን?
-
17
|1 Corintios 12:17|
አካል ሁሉ ዓይን ቢሆን መስማት ወዴት በተገኘ? ሁሉም መስማት ቢሆን ማሽተት ወዴት በተገኘ?
-
18
|1 Corintios 12:18|
አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ ብልቶችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል።
-
19
|1 Corintios 12:19|
ሁሉም አንድ ብልት ቢሆንስ አካል ወዴት በሆነ?
-
20
|1 Corintios 12:20|
ዳሩ ግን አሁን ብልቶች ብዙዎች ናቸው አካል ግን አንድ ነው።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer 2 Corintios 5-7