-
-
Amharic (NT)
-
-
6
|Lucas 22:6|
እሺም አለ፥ ሕዝብም በሌለበት አሳልፎ እንዲሰጣቸው ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር።
-
7
|Lucas 22:7|
ፋሲካንም ሊያርዱበት የሚገባው የቂጣ በዓል ደረሰ፤
-
8
|Lucas 22:8|
ጴጥሮስንና ዮሐንስንም። ፋሲካን እንድንበላ ሄዳችሁ አዘጋጁልን ብሎ ላካቸው።
-
9
|Lucas 22:9|
እነርሱም። ወዴት እናዘጋጅ ዘንድ ትወዳለህ? አሉት።
-
10
|Lucas 22:10|
እርሱም አላቸው። እነሆ፥ ወደ ከተማ ስትገቡ ማድጋ ውኃ የተሸከመ ሰው ይገናኛችኋል፤ ወደ ሚገባበት ቤት ተከተሉት፤
-
11
|Lucas 22:11|
ለባለቤቱም። መምህሩ። ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ክፍል ወዴት ነው? ይልሃል በሉት፤
-
12
|Lucas 22:12|
ያም በደርብ ላይ ያለውን የተነጠፈ ታላቅ አዳራሽ ያሳያችኋል፤ በዚያም አሰናዱልን።
-
13
|Lucas 22:13|
ሄደውም እንዳላቸው አገኙና ፋሲካን አሰናዱ።
-
14
|Lucas 22:14|
ሰዓቱም በደረሰ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር በማዕድ ተቀመጠ።
-
15
|Lucas 22:15|
እርሱም። ከመከራዬ በፊት ከእናንተ ጋር ይህን ፋሲካ ልበላ እጅግ እመኝ ነበር፤
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 31-32