-
-
Amharic (NT)
-
-
38
|1 Corintios 14:38|
ማንም የማያውቅ ቢኖር ግን አይወቅ።
-
39
|1 Corintios 14:39|
ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፥ በልሳኖች ከመናገርም አትከልክሉ፤
-
40
|1 Corintios 14:40|
ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።
-
1
|1 Corintios 15:1|
ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤
-
2
|1 Corintios 15:2|
በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ።
-
3
|1 Corintios 15:3|
እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥
-
4
|1 Corintios 15:4|
መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥
-
5
|1 Corintios 15:5|
ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ፤
-
6
|1 Corintios 15:6|
ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነርሱም የሚበዙቱ እስከ አሁን አሉ አንዳንዶች ግን አንቀላፍተዋል፤
-
7
|1 Corintios 15:7|
ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ፤
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 17-19