-
-
Amharic (NT)
-
-
18
|1 Corintios 15:18|
እንግዲያስ በክርስቶስ ያንቀላፉት ደግሞ ጠፍተዋላ።
-
19
|1 Corintios 15:19|
በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን።
-
20
|1 Corintios 15:20|
አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።
-
21
|1 Corintios 15:21|
ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና።
-
22
|1 Corintios 15:22|
ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።
-
23
|1 Corintios 15:23|
ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤
-
24
|1 Corintios 15:24|
በኋላም፥ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል።
-
25
|1 Corintios 15:25|
ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።
-
26
|1 Corintios 15:26|
የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፤
-
27
|1 Corintios 15:27|
ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን። ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 17-19