-
-
Amharic (NT)
-
-
29
|Lucas 18:29|
እርሱም። እውነት እላችኋለሁ፥ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ቤትን ወይም ወላጆችን ወይም ወንድሞችን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን የተወ፥
-
30
|Lucas 18:30|
በዚህ ዘመን ብዙ እጥፍ በሚመጣውም ዓለም የዘላለምን ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም አላቸው።
-
31
|Lucas 18:31|
አሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ ስለ ሰው ልጅም በነቢያት የተጻፈው ሁሉ ይፈጸማል።
-
32
|Lucas 18:32|
ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታልና፥ ይዘብቱበትማል ያንገላቱትማል ይተፉበትማል፤
-
33
|Lucas 18:33|
ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል።
-
34
|Lucas 18:34|
እነርሱም ከዚህ ነገር ምንም አላስተዋሉም፥ ይህም ቃል ተሰውሮባቸው ነበር፥ የተናገረውንም አላወቁም።
-
35
|Lucas 18:35|
ወደ ኢያሪኮም በቀረበ ጊዜ አንድ ዕውር እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር።
-
36
|Lucas 18:36|
ሕዝብም ሲያልፍ ሰምቶ። ይህ ምንድር ነው? ብሎ ጠየቀ።
-
37
|Lucas 18:37|
እነርሱም። የናዝሬቱ ኢየሱስ ያልፋል ብለው አወሩለት።
-
38
|Lucas 18:38|
እርሱም። የዳዊት ልጅ፥ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ እያለ ጮኸ።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 33-34