-
-
Amharic (NT)
-
-
17
|Lucas 19:17|
እርሱም። መልካም፥ አንተ በጎ ባሪያ፥ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በአሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ይሁንልህ አለው።
-
18
|Lucas 19:18|
ሁለተኛውም መጥቶ። ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አምስት ምናን አተረፈ አለው።
-
19
|Lucas 19:19|
ይህንም ደግሞ። አንተም በአምስት ከተማዎች ላይ ሁን አለው።
-
20
|Lucas 19:20|
ሌላውም መጥቶ። ጌታ ሆይ፥ በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤
-
21
|Lucas 19:21|
ፈርቼሃለሁና፥ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንህ፤ ያላኖርኸውን ትወስዳለህ ያልዘራኸውንም ታጭዳለህ አለው።
-
22
|Lucas 19:22|
እርሱም። አንተ ክፉ ባሪያ፥ አፍህ በተናገረው እፈርድብሃለሁ። እኔ ያላኖርሁትን የምወስድና ያልዘራሁትን የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ አወቅህ፤ ምን ነው ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ያልሰጠኸው?
-
23
|Lucas 19:23|
እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር አለው።
-
24
|Lucas 19:24|
በዚያም ቆመው የነበሩትን። ምናኑን ውሰዱበት አሥሩ ምናን ላለውም ስጡት አላቸው።
-
25
|Lucas 19:25|
እነርሱም። ጌታ ሆይ፥ አሥር ምናን አለው አሉት።
-
26
|Lucas 19:26|
እላችኋለሁ፥ ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፥ ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 33-34